ኢሳይያስ 60:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. “ብርሃንሽ መጥቶአልና ተነሺ አብሪ፤ የእግዚአብሔርም ክብር ወጥቶልሻል።

2. እነሆ፤ ጨለማ ምድርን፣ድቅድቅ ጨለማም ሕዝቦችን ይሸፍናል፤ነገር ግን እግዚአብሔር ወጥቶልሻል፤ክብሩንም ይገልጥልሻል።

3. ሕዝቦች ወደ ብርሃንሽ፣ነገሥታትም ወደ ንጋትሽ ጸዳል ይመጣሉ።

ኢሳይያስ 60