ኢሳይያስ 58:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. “በኀይል ጩኽ፤ ምንም አታስቀር፤ድምፅህን እንደ መለከት አሰማ፤ለሕዝቤ ዐመፃቸውን፣ለያዕቆብም ቤት ኀጢአታቸውን ተናገር።

2. ዕለት በዕለት ይፈልጉኛል፤መንገዴን ለማወቅ የሚጓጉ ይመስላሉ፤ትክክለኛውን ነገር እንደሚያደርግ፣የአምላኩንም ትእዛዝ እንዳልተወ ሕዝብ ሁሉ፣ተገቢ የሆነ ፍትሕ ይለምኑኛል፤እግዚአብሔር ወደ እነርሱ እንዲቀርብ የሚወዱም ይመስላሉ።

3. ‘አንተ ካልተቀበልኸው፣ስለ ምን ብለን ጾምን?አንተ ከጒዳይ ካልቈጠርኸው፣ስለ ምን ራሳችንን አዋረድን?’ ይላሉ።“ሆኖም በጾማችሁ ቀን የልባችሁን ታደርጋላችሁ፤ሠራተኞቻችሁንም ትበዘብዛላችሁ።

4. ጾማችሁ በጥልና በክርክር፣በግፍ ጡጫና በመደባደብ ይፈጸማል፤ከእንግዲህ ዛሬ እንደምትጾሙት ጾማችሁ፣ድምፃችሁ ወደ ላይ እንደሚሰማም ተስፋ አታድርጉ።

ኢሳይያስ 58