ኢሳይያስ 55:8-12 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

8. “ሐሳቤ እንደ ሐሳባችሁ፣መንገዴ እንደ መንገዳችሁ አይደለምና”ይላል እግዚአብሔር።

9. “ሰማያት ከምድር ከፍ እንደሚሉ፣መንገዴ ከመንገዳችሁ፣ሐሳቤም ከሐሳባችሁ እንዲሁ ከፍ ያለ ነው።

10. ዝናምና በረዶ ከሰማይ ወርዶ፣ምድርን በማራስ፣እንድታበቅልና እንድታፈራለዘሪው ዘር፣ለበላተኛም እንጀራ እንድትሰጥ ሳያደርግ፣ወደ ላይ እንደማይመለስ ሁሉ፣

11. ከአፌ የሚወጣውም ቃሌ፣በከንቱ ወደ እኔ አይመለስም፤ነገር ግን የምሻውን ያከናውናል፤የተላከበትንም ዐላማ ይፈጽማል።

12. በደስታ ትወጣላችሁ፤በሰላምም ትሸኛላችሁ፤ተራሮችና ኰረብቶች፣በፊታችሁ በእልልታ ይዘምራሉ፤የሜዳ ዛፎች ሁሉ፣ያጨበጭባሉ።

ኢሳይያስ 55