ኢሳይያስ 55:6-10 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

6. እግዚአብሔር በሚገኝበት ጊዜ ፈልጉት፤ቀርቦም ሳለ ጥሩት።

7. ክፉ ሰው መንገዱን፣በደለኛም ሐሳቡን ይተው።ወደ እግዚአብሔር ይመለስ፤ እርሱም ምሕረት ያደርግለታል፤ወደ አምላካችን ይመለስ፤ ይቅርታው ብዙ ነውና።

8. “ሐሳቤ እንደ ሐሳባችሁ፣መንገዴ እንደ መንገዳችሁ አይደለምና”ይላል እግዚአብሔር።

9. “ሰማያት ከምድር ከፍ እንደሚሉ፣መንገዴ ከመንገዳችሁ፣ሐሳቤም ከሐሳባችሁ እንዲሁ ከፍ ያለ ነው።

10. ዝናምና በረዶ ከሰማይ ወርዶ፣ምድርን በማራስ፣እንድታበቅልና እንድታፈራለዘሪው ዘር፣ለበላተኛም እንጀራ እንድትሰጥ ሳያደርግ፣ወደ ላይ እንደማይመለስ ሁሉ፣

ኢሳይያስ 55