ኢሳይያስ 55:1-2 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እናንት የተጠማችሁ ሁሉ ኑ፤እናንት ገንዘብ የሌላችሁ፣ወደ ውሆች ኑ፤ኑና ግዙ፤ ብሉም፤ኑና ያለ ገንዘብ፣ ያለ ዋጋ፣የወይን ጠጅና ወተት ግዙ።

2. ገንዘባችሁን እንጀራ ባልሆነ ነገር ላይ ለምን ታጠፋላችሁ?በማያጠግብስ ነገር ላይ ለምን ጒልበታችሁን ትጨርሳላችሁ?ስሙ፤ እኔን ስሙኝ፤ መልካም የሆነውንም ብሉ፤ነፍሳችሁም በጥሩ ምግብ ትደሰታለች።

ኢሳይያስ 55