ኢሳይያስ 54:16-17 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

16. “እነሆ የከሰሉ ፍም እንዲቀጣጠል የሚያራግበውን፣የጦር መሣሪያ የሚያበጀውን፣ አንጥረኛውን የፈጠርሁ እኔ ነኝ፤ጥፋት እንዲያደርስም የፈጠርሁ እኔ ነኝአጥፊውንም የፈጠርሁ እኔ ነኝ፤

17. በአንቺ ላይ እንዲደገን የተበጀ መሣሪያ ይከሽፋል፤የሚከስሽንም አንደበት ሁሉ ትረቺያለሽ፤እንግዲህ የእግዚአብሔር ባሪያዎች ርስት ይህ ነው፤ከእኔ የሚያገኙትም ጽድቃቸው ይኸው ነው፤”ይላል እግዚአብሔር።

ኢሳይያስ 54