ኢሳይያስ 51:19-22 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

19. እነሆ፤ በጥፋት ላይ ጥፋት መጥተውብሻል፤ታዲያ ማን ያጽናናሻል?እነርሱም መፈራረስና ጥፋት፣ ራብና ሰይፍ ናቸው፤ታዲያ ማን ያስተዛዝንሽኀሀ

20. ወንዶች ልጆችሽ ዝለዋል፤በወጥመድ እንደ ተያዘ ሚዳቋ፣በየጐዳናው አደባባይ ላይ ተኝተዋል። የእግዚአብሔር ቊጣ፣የአምላክሽም ተግሣጽ ሞልቶባቸዋል።

21. ስለዚህ አንቺ የተጐዳሽ፣ያለ ወይን ጠጅ የሰከርሽ ይህን ስሚ።

22. ሕዝቡን የሚታደግ አምላክሽ፣ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“እነሆ፤ ከእጅሽ፣ያንገደገደሽን ጽዋ ወስጃለሁ፤ያንን ጽዋ፣ የቊጣዬን ዋንጫ፣ዳግም አትጠጪውም፤

ኢሳይያስ 51