ኢሳይያስ 51:10-13 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

10. የዳኑት እንዲሻገሩ ባሕሩን፣የታላቁን ጥልቅ ውሆች ያደረቅህ፣በጥልቁም ውስጥ መንገድ ያበጀህ፣አንተ አይደለህምን?

11. እግዚአብሔር የተቤዣቸው ይመለሳሉ፤በዝማሬ ወደ ጽዮን ይገባሉ፤የዘላለማዊ ደስታን አክሊል ይቀዳጃሉ፤ተድላና ደስታ ያገኛሉ፤ሐዘንና ልቅሶም ከእነርሱ ይሸሻል።

12. “የማጽናናችሁ እኔ፣ እኔው ብቻ ነኝ፤ሟች የሆኑትን ሰዎች፣እንደ ሣር የሚጠወልጉትን የሰው ልጆችለምን ትፈራለህ?

13. የፈጠረህን፣ሰማያትን የዘረጋውን፣ምድርን የመሠረተውን እግዚአብሔርን ረስተሃል፤ሊያጠፋህ ከተዘጋጀው፣ከጨቋኙ ቊጣ የተነሣ፣በየቀኑ በሽብር ትኖራለህ፤ታዲያ የጨቋኙ ቊጣ የት አለ?

ኢሳይያስ 51