ኢሳይያስ 5:22-24 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

22. የወይን ጠጅ ለመጠጣት ጀግኖች፣የሚያሰክር መጠጥ ለመደባለቅ ብርቱ ለሆኑ ወዮላቸው!

23. ጒቦን በመቀበል በደለኛን ንጹሕ ለሚያደርጉ፣ለበደል አልባ ሰው ፍትሕን ለሚነፍጉ ወዮላቸው!

24. ስለዚህ የእሳት ነበልባል ገለባን እንደሚበላ፣ድርቆሽም በእሳት ጋይቶ እንደሚጠፋ፣የእነርሱም ሥር እንዲሁ ይበሰብሳል፤አበባቸውም እንደ ትቢያ ይበናል፤የሰራዊት ጌታ የእግዚአብሔርን ሕግ ንቀዋልና፤የእስራኤል ቅዱስ የተናገረውንም ቃል አቃለዋል።

ኢሳይያስ 5