ኢሳይያስ 5:20-23 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

20. ክፉውን መልካም፣መልካሙን ክፉ ለሚሉብርሃኑን ጨለማ፣ጨለማውን ብርሃን ለሚያደርጉ፣ጣፋጩን መራራ፣መራራውንም ጣፋጭ ለሚያደርጉ ወዮላቸው!

21. ራሳቸውን እንደ ብልኅ ለሚቈጥሩ፣በራሳቸውም አመለካከት ጥበበኛ ለሆኑ ወዮላቸው!

22. የወይን ጠጅ ለመጠጣት ጀግኖች፣የሚያሰክር መጠጥ ለመደባለቅ ብርቱ ለሆኑ ወዮላቸው!

23. ጒቦን በመቀበል በደለኛን ንጹሕ ለሚያደርጉ፣ለበደል አልባ ሰው ፍትሕን ለሚነፍጉ ወዮላቸው!

ኢሳይያስ 5