12. በግብዣቸው ላይ በገናና መሰንቆ፣ከበሮና ዋሽንት እንዲሁም የወይን ጠጅ አለ፤ነገር ግን ለእግዚአብሔር ሥራ ቦታ አልሰጡም፤ለእጆቹም ሥራ ክብር አላሳዩም።
13. ስለዚህ ሕዝቤዕውቀት በማጣቱ ይማረካል፤መኳንንቱም በራብ ይሞታሉ፤ሕዝቡም በውሃ ጥም ይቃጠላል።
14. ስለዚህ ሲኦል ሆዷን አሰፋች፣አፏንም ያለ ልክ ከፈተች፤መኳንንቱና ሕዝቡ ከረብሸኞቻቸውና ከጨፋሪዎቻቸው ጋርወደዚያ ይወርዳሉ።
15. ሰው ይዋረዳል፤የሰው ልጅም ዝቅ ዝቅ ይላል፤የእብሪተኛውም ዐይን ይሰበራል።
16. የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ግን በፍትሕ ከፍ ከፍ ይላል፤ቅዱሱም አምላክ ቅድስናውን በጽድቅ ይገልጻል።
17. በጎችም በገዛ መሰማሪያቸው እንደሚሰማሩ ሆነው ይግጣሉ፤የበግ ጠቦቶችም በባለጠጎች ፍርስራሽ ላይ ሣር ይበላሉ።
18. ኀጢአትን በማታለል ገመድ ለሚስቡ፣በደልንም በሠረገላ ማሰሪያ ለሚጐትቱ ወዮላቸው!