ኢሳይያስ 49:15-19 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

15. “እናት የምታጠባውን ልጇን ልትረሳ ትችላለችን?ለወለደችውስ ልጅ አትራራለትምን?ምናልባት እርሷ ትረሳ ይሆናል፣እኔ ግን እልረሳሽም።

16. እነሆ፤ በእጄ መዳፍ ላይ ቀርጬሻለሁ፤ቅጥሮችሽ ምንጊዜም በፊቴ ናቸው።

17. ወንዶች ልጆችሽ ፈጥነው ይመለሳሉ፤ያፈራረሱሽም ከአንቺ ይሸሻሉ።

18. ዐይንሽን ቀና አድርጊ፤ ዙሪያውንም ተመልከቺ፤ወንዶች ልጆችሽ ሁሉ ተሰብስበው ወደ አንቺ ይመጣሉ።“በሕያውነቴ እምላለሁ፤እነዚህን ሁሉ እንደ ጌጥ ትለብሻቸዋለሽ፤እንደ ሙሽራም ትጐናጸፊያቸዋለሽ” ይላል እግዚአብሔር።

19. “ፈራርሰሽ ባድማ ብትሆኚ፣ምድርሽ ፈጽሞ ቢጠፋ፣ዛሬ ለሕዝብሽ ጠባብ ብትሆኚም እንኳ፣የዋጡሽ ከአንቺ ይርቃሉ።

ኢሳይያስ 49