ኢሳይያስ 49:10-13 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

10. አይራቡም፤ አይጠሙም፤የምድረ በዳ ትኵሳት ወይም የፀሓይ ቃጠሎ አይጐዳቸውም።የሚራራላቸው ይመራቸዋል፤በውሃ ምንጭ ዳርም ያሰማራቸዋል።

11. ተራሮቼን ሁሉ መንገድ አደርጋለሁ፤ጐዳናዎቼም ከፍ ይላሉ።

12. እነሆ፤ ከሩቅ አገር ይመጣሉ፤አንዳንዶች ከሰሜን ሌሎች ከምዕራብ፣የቀሩት ደግሞ ከሲኒም ይመጣሉ።

13. ሰማያት ሆይ፤ እልል በሉ፤ምድር ሆይ፤ ደስ ይበልሽ፤ተራሮች ሆይ፤ በደስታ ዘምሩ፤ እግዚአብሔር ሕዝቡን ያጽናናል፤ለተቸገሩትም ይራራልና።

ኢሳይያስ 49