ኢሳይያስ 47:8-10 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

8. “አሁንም አንቺ ቅምጥል ፍጡር፣በራስሽ ተማምነሽ የምትቀመጪ፣በልብሽም፣‘እኔ ነኝ፣ ከእኔ በቀር ሌላ የለም፤ከእንግዲህ መበለት አልሆንም፤የወላድ መካንም አልሆንም’ የምትይ ስሚ!

9. እነዚህ ሁለት ነገሮች፣መበለትነትና የወላድ መካንነት፣አንድ ቀን ድንገት ይመጡብሻል፤የቱን ያህል አስማት፣የቱንም ያህል መተት ቢኖርሽ፣በሙሉ ኀይላቸው ይመጡብሻል።

10. በክፋትሽ ተማምነሽ፣‘ማንም አያየኝም’ አልሽ፤ደግሞም፣ ‘እኔ ነኝ፣ ከእኔ በቀር ሌላ የለም’ባልሽ ጊዜ፣ጥበብሽና ዕውቀትሽ አሳሳቱሽ።

ኢሳይያስ 47