ኢሳይያስ 46:8-12 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

8. “እናንት በደለኞች፣ ይህን አስታውሱ፤አስቡበትም፤ በልባችሁም ያዙት።

9. የጥንቱን፣ የቀደመውን ነገር አስታውሱ፤እኔ አምላክ ነኝ፤ ከእኔም በቀር ሌላ የለም፤እኔ አምላክ ነኝ፤ እንደ እኔ ያለ የለም።

10. የመጨረሻውን ከመጀመሪያው፣ገና የሚመጣውንም ከጥንቱ ተናግሬአለሁ፤‘ዐላማዬ የጸና ነው፤ደስ የሚያሰኘኝንም ሁሉ አደርጋለሁ’ እላለሁ።

11. ከምሥራቅ ነጣቂ አሞራ፣ከሩቅ ምድር ዐላማዬን የሚፈጽም ሰው እጠራለሁ።የተናገርሁትን አደርጋለሁ፤ያቀድሁትን እፈጽማለሁ።

12. እናንት እልኸኞች፣ከጽድቅም የራቃችሁ ስሙኝ።

ኢሳይያስ 46