እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“የግብፅ ሀብትና የኢትዮጵያ ንግድ፣ቁመተ ረጃጅሞቹ የሳባ ሰዎች፣ወደ አንተ ይመጣሉ፤የአንተ ይሆናሉ፤ከኋላ ይከተሉሃል፤በሰንሰለትም ታስረው ወደ አንተ በመምጣት፣በፊትህ እየሰገዱ፣‘በእውነት እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነው፤ከእርሱም በቀር ሌላ አምላክ የለም’ ብለው ይለምኑሃል።”