ሰማያት ሆይ፤ እግዚአብሔር ይህን አድርጎአልና ዘምሩ፤የምድር ጥልቆች ሆይ፤ በደስታ ጩኹ።እናንት ተራሮች፣እናንት ደኖችና ዛፎቻችሁ ሁሉ እልል በሉ፤ እግዚአብሔር ያዕቆብን ተቤዥቶአል፣በእስራኤልም ክብሩን ገልጦአልና።