ኢሳይያስ 43:25-28 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

25. “ስለ ራሴ ስል መተላለፍህን የምደመስ ስልህ፣እኔ፣ እኔው ነኝ፤ኀጢአትህን አላስባትም።

26. እስቲ ያለፈውን አስታውሰኝ፤ተቀራርበን እንከራከርበት፤ትክክለኛ ስለ መሆንህም አስረዳ።

27. የመጀመሪያው አባትህ ኀጢአት ሠርቶአል፤መምህሮችህም ዐምፀውብኛል።

28. ስለዚህ የመቅደስህን አለቆች አዋርዳለሁ፤ያዕቆብን ለጥፋት፣እስራኤልን ለስድብ እዳርጋለሁ።

ኢሳይያስ 43