ኢሳይያስ 43:17-23 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

17. እንደ ገና ላይነሡ እዚያው እንዲተኙ፣እንደ ጧፍ ኵስታሪ ረግፈው እንዲጠፉ፣ሠረገሎችንና ፈረሶችን፣ሰራዊቱንና ደጀኑን በአንድነት ያወጣ እንዲህ ይላል፤

18. “የቀደመውን ነገር አታስቡ፤ያለፈውን እርሱ።

19. እነሆ፤ አዲስ ነገር አደርጋለሁ፤እርሱም አሁን ይበቅላል፤ አታስተውሉትምን?በምድረ በዳም መንገድ አዘጋጃለሁ፤በበረሓም ምንጭ አፈልቃለሁ፤

20. የምድረ በዳ አራዊት፣ቀበሮና ጒጒት ያከብሩኛል፤በምድረ በዳ ውሃ፣በበረሓም ምንጭ እሰጣለሁና።ለመረጥሁት ሕዝቤ ውሃ እሰጣለሁ፤

21. ለራሴ ያበጀሁት ሕዝብምስጋናዬን ያውጅ ዘንድ ይህን አደርጋለሁ።

22. “ያዕቆብ ሆይ፤ አንተ ግን አልጠራኸኝም፤እስራኤል ሆይ፤ የእኔ ነገር ታክቶሃል።

23. ለሚቃጠል መሥዋዕት በጎች አላመጣህልኝም፤በመሥዋዕትህም አላከበርኸኝም።በእህል ቍርባን አላስቸገርሁህም፤በዕጣን መሥዋዕትም አላሰለቸሁህም።

ኢሳይያስ 43