ኢሳይያስ 42:16-18 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

16. ዕውሮችን በማያወቁት መንገድእመራቸዋለሁ፤ባልተለመደ ጐዳና እወስዳቸዋለሁ።ጨለማውን በፊታቸው ብርሃን አደርጋለሁ፤ጐርባጣውን ስፍራ አስተካክላለሁ።ይህን አደርጋለሁ፤አልተዋቸውም።

17. በጣዖት የሚታመኑ ግን፣ምስሎችን፣ ‘አምላኮቻችን ናችሁ’ የሚሉ፣ወደ ኋላቸው ይመለሳሉ፤ ፈጽመው ይዋረዳሉም።

18. “እናንት ደንቈሮዎች ስሙ፤እናንት ዕውሮች እዩ፤ ተመልከቱም።

ኢሳይያስ 42