ኢሳይያስ 34:14-16 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

14. የምድረ በዳ አራዊት ከጅቦች ጋር አብረው ይሆናሉ፤በበረሓ ፍየል የሚመሰሉ አጋንንትም እርስ በእርስ ይጠራራሉ፤የሌሊት ፍጥረታት ማረፊያቸውን በዚያ ያደርጋሉ፤ለራሳቸውም የማረፊያ ቦታ ያገኛሉ።

15. ጒጒት በዚያ ጐጆ ሠርታ ዕንቍላል ትጥላለች፤ትቀፈቅፋለች፤ ጫጩቶቿን በክንፎቿትታቀፋቸዋለች፤ጭላቶችም ጥንድ ጥንድ ሆነው፣ለርቢ በዚያ ይሰበሰባሉ።

16. በእግዚአብሔር መጽሐፍ እንዲህ የሚለውንተመልከቱ፤ አንብቡም፤ከእነዚህ አንዱ አይጐድልም፤እያንዳንዷም አጣማጇን አታጣም፤ይህ ትእዛዝ ከአፉ ወጥቶአል፤መንፈሱ በአንድ ላይ ይሰበስባቸዋልና።

ኢሳይያስ 34