ኢሳይያስ 34:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እናንት አሕዛብ ሆይ፤ ኑ አድምጡም፤እናንተ ሰዎች ሆይ፤ አስተውሉ።ምድርና በውስጧ ያለ ሁሉ፣ዓለምና ከእርሷ የሚበቅል ሁሉ ይስማ።

2. እግዚአብሔር አሕዛብን ሁሉ ተቈጥቶአል፤ቍጣውም በሰራዊታቸው ሁሉ ላይ ነው፤ፈጽሞ ያጠፋቸዋል፤ለዕርድም አሳልፎ ይሰጣቸዋል።

3. ከእነርሱም የተገደሉት ወደ ውጭ ይጣላሉ፤ሬሳቸው ይከረፋል፤ተራሮችም ደም በደም ይሆናሉ።

ኢሳይያስ 34