ኢሳይያስ 33:2-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

2. እግዚአብሔር ሆይ፤ ማረን፤አንተን ተስፋ አድርገናል።በየማለዳው ብርታት፣በጭንቅ ጊዜም ድነት ሁነን።

3. ሕዝቦች በድምፅህ ነጐድጓድ ይሸሻሉ፣መንግሥታት ስትነሣ ይበተናሉ።

4. ሕዝቦች ሆይ፤ አንበጣ እንደሚሰበስብ ብዝበዛችሁም ይሰበሰባል፤ሰዎችም እንደ ኩብኩባ ይጨፍሩበታል።

5. እግዚአብሔር በአርያም ተቀምጦአልና ከፍ ከፍ አለ፤ጽዮንን በጽድቅና በፍትሕ ይሞላታል።

ኢሳይያስ 33