ኢሳይያስ 31:2-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

2. እርሱም ግን ጠቢብ ነው፤ ጥፋትን ያመጣል፤ቃሉን አያጥፍም።በክፉ አድራጊዎች ቤት ላይ፣በደለኞችንም በሚረዱ ላይ ይነሣል።

3. ግብፃውያን ሰዎች እንጂ አምላክ አይደሉም፤ፈረሶቻቸውም ሥጋ እንጂ መንፈስ አይደሉም፤ እግዚአብሔር እጁን ሲዘረጋ፣ርዳታ ሰጪው ይሰናከላል፤ተረጂውም ይወድቃል፤ሁለቱም በአንድ ላይ ይጠፋሉ።

4. እግዚአብሔር እንዲህ ብሎኛል፤“አንበሳ ወይም የአንበሳ ደቦልየሰበረውን ይዞ ሲያገሣ፣ብዙ እረኞችተጠራርተው ሲመጡበት፣ጩኸታቸው እንደማያስፈራው፣በድምፃቸውም እንደማይታወክ፣የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣በጽዮን ተራራና በከፍታዎቿ ላይ ለውጊያ እንዲሁ ይወርዳል።

5. በዐናት ላይ እንደሚያንዣብቡ ወፎች፣የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ኢየሩሳሌምን እንዲሁ ይጋርዳታል፤ይከልላታል፤ ይታደጋታል፤በላይዋ ያልፋል፤ ያድናታልም።”

6. እናንተ እስራኤላውያን ሆይ፤ እጅግ ወዳ መፃችሁበት ወደ እርሱ ተመለሱ።

ኢሳይያስ 31