ኢሳይያስ 30:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. “ለዐመፀኞች ልጆች ወዮላቸው”ይላል እግዚአብሔር፤“የእኔ ያልሆነውን ሐሳብ ይከተላሉ፤ከመንፈሴ ያልሆነውን ቃል ኪዳን ያደርጋሉ፤በኀጢአት ላይ ኀጢአት ይጨምራሉ።

2. እኔን ሳይጠይቁ፣ወደ ግብፅ ይወርዳሉ፤የፈርዖንን ከለላ፣የግብፅንም ጥላ ለመጠጊያነት ይፈልጋሉ።

3. ነገር ግን የፈርዖን ከለላ ውርደት ይሆንባችኋል፤የግብፅም ጥላ ኀፍረት ያመጣባችኋል።

ኢሳይያስ 30