1. ዳዊት የሰፈረብሽ ከተማ፣አርኤል፣ አርኤል ወዮልዓመት በዓመት ላይ ጨምሪ፣ዐውደ ዓመትሽም ይቀጥል።
2. ነገር ግን አርኤልን እከባለሁ፤ታለቅሳለች፤ ዋይ ዋይ ትላለች፤ለእኔም እንደ መሠዊያ ስፍራ ትሆንልኛለች።
3. በዙሪያሽ እሰፍራለሁ፤በቅጥር እከብሻለሁ፤የከበባ ዐምባም ሠርቼ አስጨንቅሻለሁ።
4. ወደ ታች ትወርጃለሽ፤ ከምድርም በታች ትናገሪያለሽ፤ንግግርሽ ከትቢያ እየተጒተመተመ ይወጣል፤ድምፅሽ እንደ መናፍስት ድምፅ ከመሬት ወደ ላይ ይመጣል፤ንግግርሽ ከትቢያ ያንሾካሹካል።