ኢሳይያስ 28:5-8 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

5. በዚያን ቀን የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ለተረፈው ሕዝቡ፣የክብር ዘውድ፣የውበትም አክሊል ይሆናል።

6. እርሱም በፍርድ ወንበር ላይ ለሚቀመጠው፣የፍትሕ መንፈስ፣ጦርን ከከተማዪቱ በር ላይ ለሚመልሱም፣የኀይል ምንጭ ይሆናል።

7. እነዚህም በወይን ጠጅ ይንገዳገዳሉ፤በሚያሰክርም መጠጥ ይወላገዳሉ፤ካህናቱና ነቢያቱ በሚያሰክር መጠጥ ተንገደገዱ፤በወይን ጠጅ ነገር ተምታታባቸው፤በሚያሰክር መጠጥ ተወላገዱ፤ራእይ ሲያዩ ይስታሉ፤ፍርድ ሲሰጡም ይሰናከላሉ።

8. የማእድ ገበታቸው ሁሉ በትፋት ተሞልቶአል፤ከትውኪያም የጸዳ ቦታ የለም።

ኢሳይያስ 28