2. በዚያን ቀን እንዲህ ይባላል፤“ለመልካሙ የወይን ቦታ ዘምሩለት፤
3. እኔ እግዚአብሔር ጠባቂው ነኝ፤ዘወትር ውሃ አጠጣዋለሁ፤ስለዚህ ማንም አይጐዳውም፣ቀንና ሌሊት እጠብቀዋለሁ፤
4. እኔ አልቈጣም።እሾኽና ኵርንችት ምነው በተነሡብኝ!ለውጊያ በወጣሁባቸው፣አንድ ላይ ባቃጠልኋቸው!
5. አለዚያ ይምጡና መሸሸጊያቸው ያድርጉኝ፤ከእኔ ጋር ሰላም ይፍጠሩ፤አዎን፤ ከእኔ ጋር ሰላም ያድርጉ።”
6. በሚመጡት ቀናት ያዕቆብ ሥር ይሰዳል፤እስራኤልም ያቈጠቍጣል፤ ያብባልም፤በፍሬያቸውም ምድርን ሁሉ ይሞላሉ።