ኢሳይያስ 22:17-21 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

17. አንተ ኀያል ሰው ሆይ፤ ተጠንቀቅ፤ እግዚአብሔር አጥብቆ ሊይዝህ፣ በእጆቹም ጨብጦ ሊወረውርህ ነው።

18. አዙሮ አዙሮ እንደ ሩር አጡዞ፣ወደ ሰፊ አገር ይወነጭፍሃል፤አንተ የጌታህ ቤት ዕፍረበዚያ ትሞታለህ፤የክብር ሠረገሎችህም እዚያ ይቀራሉ።

19. ከማዕረግህ አወርድሃለሁ፤ከኀላፊነትህም ትባረራለህ።

20. “በዚያን ቀን አገልጋዬን፣ የኬልቅያስን ልጅ ኤልያቄምን እጠራለሁ፤

21. መጐናጸፊያህን አለብሰዋለሁ፤ መታጠቂያህን አስታጥቀዋለሁ፤ ሥልጣንህንም አስረክበዋለሁ። እርሱም በኢየሩሳሌም ለሚኖሩ፣ ለይሁዳም ቤት አባት ይሆናል።

ኢሳይያስ 22