ኢሳይያስ 14:7-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

7. ምድር ሁሉ ሰላምና ዕረፍት አግኝታለች፤የደስታም ዝማሬ ታስተጋባለች።

8. ጥድና የሊባኖስ ዝግባ እንኳ ደስ ብሎአቸው፣“አንተም ወደቅህ፤ዕንጨት ቈራጭምመጥረቢያ አላነሣብንምቃ አሉ።

9. በመጣህ ጊዜሲኦል ልትቀበልህ ተነሣሥታለች፤ይቀበሉህም ዘንድ የሙታንን መናፍስት፣በዓለም ገዥ የነበሩትን ሁሉ ቀስቅሳለች፤በአሕዛብ ላይ የነገሡትን ነገሥታትከዙፋናቸው አውርዳለች።

ኢሳይያስ 14