ኢሳይያስ 14:6-10 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

6. ሕዝቦችን በማያቋርጥ ቍጣ የመታውን፣ያለ ርኅራኄ እያሳደደየቀጠቀጠውን ሰብሮአል።

7. ምድር ሁሉ ሰላምና ዕረፍት አግኝታለች፤የደስታም ዝማሬ ታስተጋባለች።

8. ጥድና የሊባኖስ ዝግባ እንኳ ደስ ብሎአቸው፣“አንተም ወደቅህ፤ዕንጨት ቈራጭምመጥረቢያ አላነሣብንምቃ አሉ።

9. በመጣህ ጊዜሲኦል ልትቀበልህ ተነሣሥታለች፤ይቀበሉህም ዘንድ የሙታንን መናፍስት፣በዓለም ገዥ የነበሩትን ሁሉ ቀስቅሳለች፤በአሕዛብ ላይ የነገሡትን ነገሥታትከዙፋናቸው አውርዳለች።

10. እነርሱ ሁሉ ይመልሱልሃል፤እንዲህም ይሉሃል፤“አንተም እንደ እኛ ደከምህ፤እንደ እኛም ሆንህ።”

ኢሳይያስ 14