23. ገዥዎችሽ ዐመፀኞችናየሌባ ግብረ ዐበሮች ናቸው፤ሁሉም ጒቦን ይወዳሉ፤እጅ መንሻንም በብርቱ ይፈልጋሉ፤አባት ለሌላቸው አይቆሙም፤የመበለቶችንም አቤቱታ አይሰሙም።
24. ስለዚህ ጌታ፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣የእስራኤል ኀያል እንዲህ ይላል፤“በባላንጣዎቼ ላይ ቍጣዬን እገልጣለሁ፤ጠላቶቼንም እበቀላለሁ።
25. እጄን በአንቺ ላይ አነሣለሁ፣ዝገትሽን ፈጽሜ አጠራለሁ፤ጒድፍሽንም ሁሉ አስወግዳለሁ።
26. ፈራጆችሽን እንደ ጥንቱ፣አማካሪዎችሽንም እንደ ቀድሞው እመልሳለሁ፤ከዚያም የጽድቅ መዲና፣የታመነች ከተማተብለሽ ትጠሪያለሽ።
27. ጽዮን በፍትሕ፣በንስሓ የሚመለሱ ነዋሪዎቿም በጽድቅ ይዋጃሉ።
28. ዐመፀኞችና ኀጢአታኞች ግን በአንድነት ይደቃሉ፤ እግዚአብሔርንም የሚተዉ ይጠፋሉ።
29. “ደስ በተሰኛችሁባቸው የአድባር ዛፎችታፍራላችሁ፤በመረጣችኋቸውም የአትክልት ቦታዎችትዋረዳላችሁ።
30. ቅጠሉ እንደ ጠወለገ ወርካ፣ውሃም እንደሌለው የአትክልት ቦታ ትሆናላችሁ።
31. ብርቱ ሰው እንደ ገለባ፣ሥራውም እንደ ብልጭታ ይሆናል፤ሁለቱም አብረው ይቃጠላሉ፤እሳቱንም የሚያጠፋው የለም።