ኢሳይያስ 1:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. በይሁዳ ነገሥታት በዖዝያን፣ በኢዮአታም፣ በአካዝና በሕዝቅያስ ዘመን፣ የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ ስለ ይሁዳና ስለ ኢየሩሳሌም ያየው ራእይ፤

2. ሰማያት ሆይ፤ ስሙ! ምድር ሆይ፤ አድምጪ! እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ተናግሮአልና፤“ልጆች ወለድሁ፣ አሳደግኋቸውም፤እነርሱ ግን ዐመፁብኝ።

3. በሬ ጌታውን፣አህያ የባለቤቱን ጋጥ ያውቃል፤እስራኤል ግን አላወቀም፤ሕዝቤም አላስተዋለም።”

4. እናንተ ኀጢአተኛ ሕዝብ፣በደል የሞላበት ወገን፣የክፉ አድራጊ ዘር፣ምግባረ ብልሹ ልጆች ወዮላችሁ እግዚአብሔርን ትተዋል፤የእስራኤልን ቅዱስ አቃለዋል፤ጀርባቸውንም በእርሱ ላይ አዙረዋል።

5. ለምን ዳግመኛ ትመታላችሁ?ለምንስ በዐመፅ ትጸናላችሁ?ራሳችሁ በሙሉ ታሞአል፤ልባችሁ ሁሉ ታውኮአል።

ኢሳይያስ 1