አብድዩ 1:8-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

8. “በዚያ ቀን ጥበበኛ ሰዎችን ከኤዶም፣አስተዋዮችንም ከዔሳው ተራሮች አልደመስስምን?”ይላል እግዚአብሔር።

9. ቴማን ሆይ፤ ተዋጊዎችህ ይደነግጣሉ፤በዔሳውም ተራሮች ያለ ሁሉ፣ተገድሎ ይጠፋል።

10. በወንድምህ በያዕቆብ ላይ ስላደረግኸው ግፍ፣በዕፍረት ትሸፈናለህ፤ለዘላለምም ትጠፋለህ።

11. እንግዶች ሀብቱን ዘርፈው ሲሄዱ፣ባዕዳንም በበሮቹ ሲገቡ፣በኢየሩሳሌምም ላይ ዕጣ ሲጣጣሉ፣በዚያ ቀን ገለልተኛ ሆነህ ተመለከትህ፣አንተም ከእነርሱ እንደ አንዱ ሆንህ።

አብድዩ 1