አስቴር 8:5-7 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

5. እንዲህም አለች፤ “ንጉሡን ደስ የሚያሰኘውና እኔም በፊቱ ሞገስ አግኝቼ ከሆነ፣ ጉዳዩም በንጉሡ ዘንድ ተገቢ ሆኖ ከተገኘና በእኔም ደስ ከተሰኘ፣ የአጋጋዊው የሐመዳቱ ልጅ ሐማ በንጉሡ አውራጃዎች ሁሉ የሚገኙትን አይሁድ ለማጥፋት የሸረበውን ሤራና የጻፈውን ደብዳቤ የሚሽር ትእዛዝ ይጻፍ።

6. በሕዝቤ ላይ መዐት ሲወርድ እያየሁ እንዴት ልታገሥ እችላለሁ? የቤተ ሰቤንስ መጥፋት እያየሁ እንዴት መቋቋም እችላለሁ?”

7. ንጉሥ ጠረክሲስም ለንግሥት አስቴርና ለአይሁዳዊው ለመርዶክዮስ እንዲህ ሲል መለሰላቸው፤ “እነሆ ሐማ አይሁድን ለማጥፋት ስላቀደ፣ ቤት ንብረቱን ለአስቴር ሰጥቻለሁ፤ እርሱንም በዕንጨት ላይ ሰቅለውታል።

አስቴር 8