1. ከዚህ በኋላ ንጉሡ ጠረክሲስ ቊጣው ሲበርድለት አስጢንን፣ ያደረገችውን ነገርና በእርሷም ላይ ያስተላለፈውን ዐዋጅ ዐሰበ።
2. ከዚያም የንጉሡ የቅርብ አገልጋዮች እንዲህ የሚል ሐሳብ አቀረቡ፤ “ለንጉሡ ቈንጆ ልጃገረዶች ይፈለጉለት፤
3. እነዚህን ሁሉ ቈንጆ ልጃገረዶች በሱሳ ግንብ ወደሚገኘው ልዩ የሴቶች መኖሪያ ቦታ እንዲያመጡ፣ ንጉሡ በግዛቱ በሚገኙት አውራጃዎቹ ሁሉ ባለ ሥልጣኖችን ይሹም፤ እነርሱም የሴቶች የበላይ ኀላፊ በሆነው በንጉሡ ጃንደረባ በሄጌ ኀላፊነት ሥር ይሁኑ፤ የውበትም እንክብካቤ ይደረግላቸው።
4. ከዚያም ንጉሡን ደስ የምታሰኘው ልጃገረድ በአስጢን ፈንታ ንግሥት ትሁን።” ምክሩ ንጉሡን ደስ አሰኘው፤ በተባለውም መሠረት አደረገ።