አሞጽ 9:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ጌታን በመሠዊያው አጠገብ ቆሞ አየሁት፤ እርሱም እንዲህ አለ፤“መድረኮቹ እንዲናወጡ፣ጒልላቶቹን ምታ፣በሕዝቡም ሁሉ ራስ ላይ ሰባብራቸው፤የቀሩትን በሰይፍ እገድላቸዋለሁ፤ከእነርሱ አንድም ሰው አይሸሽም፤ቢሸሽም የሚያመልጥ የለም።

2. መቃብር በጥልቀት ቈፍረው ቢወርዱም፣እጄ ከዚያ ታወጣቸዋለች፤ወደ ሰማይ ቢወጡም፣ከዚያ አወርዳቸዋለሁ።

3. በቀርሜሎስ ጫፍ ላይ ቢሸሸጉም፣አድኜ ፈልጌ ከዚያ አወርዳቸዋለሁ፤እይዛቸዋለሁም፤በጥልቅ ባሕር ውስጥ ከእኔ ቢሸሸጉም፣በዚያ እባቡ እንዲነድፋቸው አዘዋለሁ፤

አሞጽ 9