9. “የይስሐቅ ማምለኪያ ኮረብታዎች ባድማ ይሆናሉ፤የእስራኤል መቅደሶች ይፈርሳሉ፤በኢዮርብዓምም ቤት ላይ በሰይፌ እነሣለሁ።”
10. ከዚህ በኋላ የቤቴል ካህን አሜስያስ ወደ እስራኤል ንጉሥ ወደ ኢዮርብዓም እንዲህ ሲል መልእክት ላከ፤ “አሞጽ በእስራኤል ቤት መካከል በአንተ ላይ እያሤረ ነው፤ ምድሪቱም ቃሉን ሁሉ ልትሸከም አትችልም፤
11. አሞጽ እንዲህ ሲል ተናግሮ ነበርና፤“ ‘ኢዮርብዓም በሰይፍ ይሞታል፤እስራኤልም በእርግጥ ከትውልድ አገሩተማርኮ ይሄዳል።”
12. አሜስያስም፣ አሞጽን እንዲህ አለው፤ “አንተ ባለ ራእይ ከዚህ ሂድ! ከይሁዳ ምድር ሽሽ፤ እዚያም እንጀራህን ብላ፤ በዚያም ትንቢት ተናገር።