1. በጽዮን ተዘልላችሁ የምትቀመጡ፣በሰማርያ ተራራ ያለ ሥጋት የምትኖሩ፣የእስራኤልም ሕዝብ ለርዳታ ወደ እናንተ የሚመጡባችሁ፣እናንት የአሕዛብ አለቆች ሆይ፤ ወዮላችሁ!
2. ወደ ካልኔ ሂዱ፤ እርሱንም ተመልከቱ፤ከዚያም ወደ ታላቂቱ ሐማት ሂዱ፤ወደ ፍልስጥኤም ከተማ ወደ ጌትም ውረዱ፤እነዚህ ከሁለቱ መንግሥታቶቻችሁ ይሻላሉን?የምድራቸውስ ስፋት ከእናንተ ይበልጣልን?
3. ክፉውን ቀን ለምታርቁ፣የግፍንም ወንበር ለምታቀርቡ ወዮላችሁ!