ናሆም 2:6-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

6. የወንዙ በር ወለል ብሎ ተከፈተ፤ቤተ መንግሥቱም ወደቀ።

7. ከተማዪቱ መማረኳና መወሰዷ እንደማይቀር፣አስቀድሞ ተነግሮአል፤ሴቶች ባሪያዎቿ እንደ ርግብ ያለቅሳሉ፤ደረታቸውንም ይደቃሉ።

8. ነነዌ እንደ ኵሬ ናት፤ውሃዋም ይደርቃል፤“ቁም! ቁም!” ብለው ይጮኻሉ፤ነገር ግን ወደ ኋላ የሚመለስ የለም።

9. ብሩን ዝረፉ፤ወርቁን ንጠቍ፤በየግምጃ ቤቱ ያለው፤የተከማቸውም ሀብት ስፍር ቍጥር የለውም።

ናሆም 2