71. ከየቤተ ሰቡ አባቶችም አንዳንዶች ለሥራው የሚሆን 20,000 የወርቅ ዳሪክ 2,200 የብር ምናን ለግምጃ ቤቱ ሰጡ።
72. የቀረው ሕዝብ ባጠቃላይ የሰጠው 20,000 የወርቅ ዳሪክ 2,000 የብር ምናንና 67 አልባሰ ተክህኖ ነበር።
73. ካህናቱ፣ ሌዋውያኑ፣ በር ጠባቂዎቹ፣ መዘምራኑና የቤተ መቅደሱ አገልጋዮች፣ ከሕዝቡም የተወሰነው ክፍልና የቀሩት እስራኤላውያን በየራሳቸው ከተሞች ሰፈሩ።ሰባተኛው ወር በደረሰና እስራኤላውያን ሁሉ በየከተሞቻቸው በተቀመጡ ጊዜ፣