በዚያን ቀን ስጦታው፣ በኵራቱና ዐሥራቱ የሚቀመጥበት ዕቃ ቤት የሚጠብቁ ሰዎች ተሾሙ። እነርሱም በየከተሞች ዙሪያ ከሚገኙት የእርሻ ቦታዎች ሕጉ በሚያዘው መሠረት የካህናቱንና የሌዋውያኑን ድርሻ ወደ ዕቃ ቤቱ ማምጣት ነበረባቸው፤ ይሁዳ በሚያገለግሉ ካህናትና ሌዋውያን ደስ ተሰኝተው ነበርና።