ቲቶ 3:13-15 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

13. ሕግ ዐዋቂውን ዜማስንና አጵሎስን በጒዟቸው ለመርዳት የተቻለህን ሁሉ አድርግ፤ የሚያስፈልጋቸውንም ሁሉ አሟላላቸው።

14. ከእኛ ወገን ለሆኑት ለዕለት የሚያስፈልጋቸውን እንዲያገኙና ኑሮአቸውም ፍሬ የሌለው እንዳይሆን ለመልካም ሥራ መትጋትን ይማሩ ዘንድ ይገባቸዋል።

15. ከእኔ ጋር ያሉት ሁሉ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል። ከእምነት የተነሣ ለሚወዱን ሰላምታ አቅርቡልን።ጸጋ ከሁላችሁ ጋር ይሁን።

ቲቶ 3