3. ሹሞቿ የሚያገሡ አንበሶች፣ገዦቿ ለነገ የማይሉ፣የምሽት ተኵላዎች ናቸው።
4. ነቢያቷ ትዕቢተኞች፣አታላዮችም ናቸው፤ካህናቷ መቅደሱን ያረክሳሉ፣በሕግም ላይ ያምፃሉ።
5. በእርሷ ውስጥ ያለው እግዚአብሔር ጻድቅ ነው፤ፈጽሞ አይሳሳትም፤በየማለዳው ቅን ፍርድ ይሰጣል፤በየቀኑም አይደክምም፤ዐመፀኞች ግን ዕፍረት አያውቁም።
6. “ሕዝቦችን አጥፍቻለሁ፤ምሽጋቸው ተደምስሶአል፤ማንም እንዳያልፍባቸው፣መንገዳቸውን ባድማ አደረግሁ፤ከተሞቻቸው ተደምስሰዋል፤አንድም ሰው የለም፤ ነዋሪም ከቶ አይገኝባቸውም።