ሶፎንያስ 3:19-20 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

19. በዚያ ጊዜ፣ያስጨነቁሽን ሁሉ እቀጣለሁ፤አንካሶችን እታደጋለሁ፤የተበተኑትንም እሰበስባለሁ፤በተዋረዱበት ምድር ሁሉ፣ለውዳሴና ለክብር አደርጋቸዋለሁ።

20. በዚያን ጊዜ እሰበስባችኋለሁ፤ያን ጊዜ ወደ አገራችሁ እመልሳችኋለሁ፤ዐይናችሁ እያየ፣ምርኮአችሁን በምመልስበት ጊዜ፣መከበርንና መወደስን፣በምድር ሕዝብ ሁሉ መካከል እሰጣችኋለሁ”፤ይላል እግዚአብሔር።

ሶፎንያስ 3