13. ሀብታቸው ይዘረፋል፤ቤታቸው ይፈራርሳል፤ቤቶች ይሠራሉ፤ነገር ግን አይኖሩባቸውም፤ወይን ይተክላሉ፤ጠጁን ግን አይጠጡም።
14. “ታላቁ የእግዚአብሔር ቀን ቅርብ ነው፤ቅርብ ነው ፈጥኖም ይመጣል፤ በእግዚአብሔር ቀን የሚሰማው ልቅሶ መራራ ነው፤በዚያ ጦረኛውም ምርር ብሎ ይጮኻል፤
15. ያ ቀን የመዓት ቀን፣የመከራና የጭንቀት ቀን፣የሁከትና የጥፋት ቀን፣የጨለማና የጭጋግ ቀን፣የደመናና የድቅድቅ ጨለማ ቀን ይሆናል፤
16. ያ ቀን በተመሸጉ ከተሞችና፣በረጃጅም ግንቦች ላይ፣የመለከት ድምፅና የጦርነት ጩኸት የሚሰማበት ቀን ይሆናል።
17. እንደ ዕውር እንዲራመዱ፣በሰዎች ላይ ጭንቀት አመጣባቸዋለሁ፤ በእግዚአብሔር ላይ ኀጢአትን ሠርተዋልና።ደማቸው እንደ ትቢያ፣ሥጋቸውም እንደ ጒድፍ ይጣላል።