1. በይሁዳ ንጉሥ በአሞጽ ልጅ በኢዮስያስ ዘመን ወደ ሕዝቅያስ ልጅ፣ ወደ አማርያ ልጅ፣ ወደ ጎዶልያስ ልጅ፣ ወደ ኵሲ ልጅ ወደ ሶፎንያስ የመጣ የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው፤
2. “ማንኛውንም ነገር፣ከምድር ገጽ አጠፋለሁ”ይላል እግዚአብሔር።
3. “ሰውንና እንስሳን አጠፋለሁ፤የሰማይን ወፎች፣የባሕርንም ዓሦች አጠፋለሁ፤ሰውን ከምድር ገጽ በማስወግድበት ጊዜ፣ክፉዎች የፍርስራሽ ክምር ይሆናሉ”ይላል እግዚአብሔር።
4. “እጄን በይሁዳ፣በኢየሩሳሌምም በሚኖሩት ሁሉ ላይ አነሣለሁ፤የበኣልን ትሩፍ፣የጣዖታቱንና የአመንዝራ ካህናቱን ስም ሁሉ ከዚህ ስፍራ አጠፋለሁ፤