ሰቆቃወ 5:9-13 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

9. በምድረ በዳ ካለው ሰይፍ የተነሣ፣በሕይወታችን ተወራርደን እንጀራ አገኘን።

10. ቈዳችን እንደ ምድጃ ጠቍሮአል፤በራብም ተቃጥሎአል።

11. ሴቶች በጽዮን፣ደናግል በይሁዳ ከተሞች ተደፈሩ።

12. መሳፍንት በእነርሱ እጅ ተሰቀሉ፤ሽማግሌዎችም አልተከበሩም።

13. ጐልማሶች ወፍጮ እንዲፈጩ ተገደዱ፤ወንዶች ልጆች በዕንጨት ሸክም ተንገዳገዱ።

ሰቆቃወ 5