ሰቆቃወ 5:4-7 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. ለምንጠጣው ውሃ መክፈል ነበረብን፤ዕንጨታችንንም የምናገኘው በግዢ ነበር።

5. የሚያሳድዱን ከተረከዞቻችን ሥር ናቸው፤ተጨንቀናል ዕረፍትም አጥተናል።

6. እንጀራ እንጠግብ ዘንድ፣ለአሦርና ለግብፅ እጃችንን ሰጠን።

7. አባቶቻችን ኀጢአት ሠርተው አለፉ፤እኛም የእነርሱን ቅጣት ተሸከምን።

ሰቆቃወ 5