ሰቆቃወ 4:16-19 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

16. እግዚአብሔር ራሱ በትኖአቸዋል፤ከእንግዲህ ወዲያ አይጠብቃቸውም፤ካህናቱ አልተከበሩም፤ሽማግሌዎቹም ከበሬታ አላገኙም።

17. ከሁሉም በላይ በከንቱ ርዳታን ስንጠባበቅ፣ዐይኖቻችን ደከሙ፤ከግንብ ማማችን ላይ ሆነን፣ሊያድን ከማይችል ሕዝብ ርዳታ ጠበቅን።

18. ሰዎች እግር እግራችንን ተከታተሉን፤ስለዚህ በመንገዳችን መሄድ አልቻልንም፤መጨረሻችን ቀርቦአል፤ ቀኖቻችንም ተቈጥረዋል፤ፍጻሜያችን መጥቶአልና።

19. ከሰማይ ንስሮች ይልቅ፣ጠላቶቻችን ፈጣኖች ናቸው፤በተራሮች ላይ አሳደዱን፤በምድረ በዳም ሸመቁብን።

ሰቆቃወ 4